ልጆች ወደ ቀዶ ሕክምና ክፍል ሲወሰዱ ራሳቸው የሚነዷቸው መኪኖች ስራ ላይ ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የሳን ዲዬጎ የሕፃናት ሆስፒታል ልጆች ወደ ቀዶ ህክምና ክፍል ሲገቡ ራሳቸው እያሽከረከሯቸው የሚሄዱ ቅንጡና ዘመናዊ አነስተኛ መኪኖችን ስራ ላይ አውሏል።

መኪኖቹ በቴክኖሎጂ አማካኝነት( remote controlled) ቁጥጥር የሚደረግባቸው ናቸው።

እነዚህ በሕጻናት ሆስፒታል ውስጥ ያሉት መኪኖች በረዳት ሃኪሞች ወይም በሐኪሞች ቁጥጥር የሚደረግላቸው ሲሆን፥ ህፃናቱ ህሙማን ወደ ቀዶ ሕክምና ክፍል

ከምግባታቸው በፊት ራሳቸውን ዘና እንዲሉ የተዘጋጀ ፕሮግራም አካል ናቸው።

በዚህ መርሃ ግብረ ህፃናት ደስተኛ ሲሆኑ፥ ወላጆቻቸውም ዘና ብለው የልጆቻቸውን ዘና ማለት ሲያዩ መደሰታቸውን የህክምና ባለሙያዎች ተናግረዋል።

ልጆች ወደ ቀዶ ህክምና ክፍል ውስጥ ሲጓዙ ምቾት እንዲሰማቸው በሚል የቢ.ኤም.ደብሊዩ፣ መርሰዲስ ወይም ላምቦርጊኒ ዓይነት በምቾታቸው የታወቁ መኪኖች ናቸው በሆስፒታሉ አገልግሎት ላይ የዋሉት።

መኪናዎቹ ከሳን ድዬጎ ክልል አንድ የህግ አስፈፃሚ የተበረከቱ መሆናቸውም ተጠቁሟል።

 

 

 

ምንጭ፥ ሮይተርስ