እንግሊዛዊው ዲዛይነር ከልጆች ጋር የሚያድግ ልብስ ሰርቷል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) እንግሊዛዊው ዲዛይነር የሰራው ከህጻናት ልጆች የሰውነት መጠን ጋር እያደገ በሚሄድ ልብስ የብሪቴይን ጄምስ ደይሰን ሽልማትን አሸንፏል።

ህጻናት በመጀመሪያ ሁለት ዓመታት እድሜያቸው በፍጥነት የሚያድጉ እና ቁመታቸው የሚጨምር ሲሆን፥ እድሜያቸው 3 ዓመት ከመድረሱ በፊትም ለልብሳቸው በርካታ ገንዘብ ይወጣል።

ይህ በወላጆች ላይ የሚያሳድረው ጫና እና በዚህ ጊዜ ውስጥ የሚጣሉት ለብሶች የሚፈጥሩት ቆሻሻ ያሳሰበው የ24 ዓመቱ ራያን ያሲን በዚህ ዙሪያ አዲስ ነገር ለመፍጠር ይወስናል።

ከለንደን ሮያል ኮሌጅ የጥበባት ትምህር ቤት በቅርቡ የተመረቀው ራያን፥ ህጻናት ልጆች እያደጉ በሚሄዱበት ጊዜ መጠኑ አብሮ የሚጨምር ወይም አብሮ የሚያድግ ልብስ ወደ መስራትም ይገባል።

በዚህም ተለጣጭ ጨርቆጥን በመጠቀም ከህጻናት ልጆች የሰውነት እድገት ጋር አብሮ እያደገ የሚሄድ ልብስ መስራት መቻሉ ነው የተነገረው።

grow_with_childeren_2.jpeg

በአሁኑ ጊዜ ራያን ሁለት ከህጻናት ልጆች ጋር የሚያድግ ሁለት አይነት ሱሪዎችን እና ጃኬት የሰራ ሲሆን፥ ወደ ፊትም ይህንን ስራውን የበለጠ ማስፋፋት እንደሚፈለግ አስታውቋል።

ምንጭ፦ www.huffingtonpost.co.uk