በኒውዚላንድ አንዲት ከተማ ከቆሻሻ በሚመነጭ የኤሌክትሪክ ሃይል የሚንቀሳቀስ የቆሻሻ ማንሻ ተሽከርካሪን ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በኒውዚላንድ የክራይስትቸርች ከተማ ከቆሻሻ በሚመነጭ የኤሌክትሪክ ሃይል የሚንቀሳቀስ የመጀመሪያውን ተሽከርካሪ ወደ ስራ ማስገበቷን የሀገሪቱ የፅዳት አስዳደር ተቋም ገለፀ።

በፅዳት አስተዳደሩ የሚሰበሰበው ቆሻሻ አዲሱን የአሌክትሪክ ተሽከርካሪ ለማንቀሳቀስ ሃይል ለመሙላት ያገልግላል ተብሏል።

ከተማዋ በደቡብ የሀገሪቱ ንፍቀ ክበብ በቆሻሻ የሚንቀሳቀስ የቆሻሻ ማንሻ ተሽከርካሪ ባለቤት በመሆን ቀዳሚዋ እንደምትሆን ነው የተነገረው።

የፅዳት አስተዳደሩ ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ ቶም ኒከልስ፥ የኔዘርላንዱ EMOSS ኩባንያ በ2017 መጀመሪያ ላይ በቀጣይ በኦክላንድ መሃል የገበያ አካባቢዎች የሚጣሉ ቆሻሻዎችን የሚያነሳ ተሽከርካሪ መገጣጠም መጀመሩን ተናግረዋል።

ተቋማቸው በአሁኑ ወቅት በኤሌክትሪክ ሃይል የሚንቀሳቀሱ 23 አነስተኛ ተሽከርካሪዎችን እየተጠቀምን ነው ብለዋል።

አዲሱ ተሸከርካሪም አንድ ጊዜ ከቆሻሻ በተሰበሰበ የኤሌክትሪክ ሃይል ከተሞላ በኋላ 200 ኪሎሜትሮችን በመዞር ቆሻሻ መሰብሰብ እንደሚችል ነው የተነገረለት።

የመጀመሪያው ተሽከርካሪ የኔዘርላንድስ ኩባንያ ከሆነው EMOSS በቀጥታ ተገጣጥሞ የመጣ በመሆኑ ዋጋው ከፍተኛ መሆኑን የፅዳት አስተዳደሩ ዳይሬክተር ገልፀዋል።

በሚቀጥሉት 12 ወራት ውስጥ በኒውዚላንደ የኩባንያው ተወካይ በመሆን በቅናሽ ዋጋ ተሽከርካሪዎችን ለማምጣት ጥረት እያደረግን ነው ብለዋል።

የፅዳት አስተዳደሩ ከቆሻሻ ከሚሰበሰበው ሃይል በሀገር ደረጃ 18 ሺህ ቤቶች ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁሟል።

የቆሻሻ መሰብሰቢያ ተሸከርካሪው 16 ቶን የመጫን አቅም አለው።

በክራይስትቸርች ከተማ ከሚሰበሰበው ቆሻሻም እስከ 6 ሺህ ኪሎዋት ሀይል በማመንጨት ተሽከርካሪው በቂ ሃይል የሚያገኝ ይሆናል።

ከዚህም ባሻገር በየቀኑ 275 ቤቶች ተጠቃሚ ማድረግ ይቻላል ነው የተባለው።

 

 

 

 

 

www.stuff.co.nz