ቲ ሞባይል አዲስ የአንድሮይድ ስማርት ስልክ ይዞ መጥቷል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቲ ሞባይል ቀደም ባሉ ጊዜያት ከሚታወቁ የሞባይል ስልኮች መጠሪያዎች ውስጥ አንዱ ነበር።

ኩባንያው በትናንትናው እለት “ሬቨቨል (Revvl)” የተባለ አዲስ የአንድሮይድ ስማርት ስልክ ይዞ ዳግም ወደ ገበያው ሊመለስ መሆኑን አረጋግጧል።

“ሬቨቨል (Revvl)” የሚል መጠሪያ የተሰጠው አዲሱ የቲ ሞባይል ስማርት ስልክ አድሮይድ ኖውገት ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚጠቀም መሆኑም ተገልጿል።

አዲሱ ስማርት ስልክ 5 ነጥብ 5 ኢንች የስክሪን ስፋት ሲኖረው፥ 32 ጊጋ ባይት ራም እና 23 ጊጋ ባይት የመረጃ መያዣ (ስቶሬጅ) አለው ተብሏል።

ከጀርባው 13 ሚጋ ፒክስል እንዲሁም ከፊት 5 ሜጋ ፒክስል ጥራት ያላቸው ካሜራዎች እንደተገጠሙለትም ተነግሯል።

በተጨማሪም ስልኩን በጣታችን አሻራ መቆለፍ ያስችለናልም ተብሏል።

ስልኩ በአነስተኛ ዋጋ እንደቀረበ እየተነገረ ሲሆን፥ በተለይም የቲ ሞባይል ደንበኞች ስልኩን የግላቸው ለማድረግ በወር 5 የአሜሪካ ዶላር ብቻ መክፈል ነው የሚጠበቅባቸው።

ኩባንያው “ሬቨቨል (Revvl)” የተባለውን ስማርት ስልኩን ከዛሬ ጀምሮ ለገበያ የሚያቀርብ መሆኑም ተገልጿል።

ምንጭ፦ fossbytes.com