ዩ ትዩብ አዲስ የመልእክት መላላኪያ “ዩ ትዩብ ቻት” አገልግሎት አስተዋወቀ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 2፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ግዙፉ የቪዲዮ ማጫወቻ ዩ ትዩብ ተጠቃሚዎቹ ወደ ላሌ ድረ ገጽ መሄድ ሳያስፈልጋቸው እርስ በእርስ ለመነጋጋር የሚያስችላቸው አዲስ አገልግሎት ማቅረቡን አስታውቋል።

“ሼር ኦን ዩ ትዩብ (Share on YouTube)” የሚል መጠሪያ የተሰጠው አዲሱ የዩ ትዩብ አገልግሎት በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ለሚገኙ የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች ይፋ መደረጉም ተነግሯል።

አዲሱ የመልእክት መላላኪያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቪዲዮ ለመላላክ እና ስለቪዲዮ ለመነጋገር የዩ ትዩብን በመዝጋት እንደ ሜሴንጀር ያሉ ወደ ሌሎች መተግበሪያዎች የሚያደርጉትን ጉዙ እንደሚያስቀር ተስፋ ተጥሎበታል።

የዩ ትዩብ ኩባንያ አዲሱ አገልግሎቱን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በግንቦት ወር 2016 ላይ ነበር መስራት እንደጀመረ የተነገረው።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በያዝነው 2017 የመጀሪያ ወራት ደግሞ በካናዳ ሙከራ ሲያደርግበት ቆይቷል።

የዩ ትዩብ ኩባንያ የምርት ሃላፊ ቤኖይት ዴቦውርስቴይ በኩባንያው ብሎግ ፖስት ላይ ተጠቃሚዎች ከዛሬው እለት ጀምረው አገልግሎቱን መጠቀም ይችላሉ ብለዋል።

አዲስ በተዋወቀው መተግበሪያው ቪዲዮ መላላክ ብቻ ሳይሆን ስለ ቪዲዮዎቹ በፅሁፍ መነጋጋር፣ በሌላ ቪዲዮ ምላሽ መስጠት እና ሌሎች ጓደኞቻችን ከእኛ ጋር እንዲጋገሩ መጋበዝም ያስችላል።

“አዲሱ ዩ ትዩብ ሼር በኢንተርኔት ላይ ቪዲዩ መጋራትን ቀላል፣ ፈጣን እና አዝናኝ እንደሚያደርግ ተስፋ አለን ሲሉም” ኩባንያ የምርት ሃላፊ ቤኖይት ዴቦውርስቴይ ተናግረዋል።

የዩ ትዩብ ቻት አገልግሎት በአሁኑ ጊዜ ለሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች ብቻ የቀረበ ሲሆን፥ ለዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር ተጠቃሚዎችስ ለሚለው እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።

አገልግሎቱን ዩ ትዩብ ላይ በሚገኘው ሼር (Share) ቁልፍ አማካኝነት የምናገኝ ሲሆን፥ ሼር የሚለውን ቁልፍ በምንነካበት ጊዜም በስልካችን ላይ ከመዘገብናቸው ስዎች ስም ዝርዝር ውስጥ የምልክላቸውን በመምረጥ መላክ ያስችለናል።

ShareOnYoutube-796x429.jpg

በአገልግሎቱም አንድ ለአንድ አሊያም እስከ 30 ሰዎችን በሚያቅፍ የቡድን መነጋገሪያ መልእክት ለመላላክ የሚያስችለን ሲሆን፥ በጽሁፍ እና በኢሚጆዎች ጭምር እዚያው ላይ መልስ መስጠትም ያስችለናል።

ምንጭ፦ www.dailymail.co.uk