የጋናው ክዋሜ ንክሩማህ ዩኒቨርሲቲ በፀሐይ ሃይል የምትንቀሳቀስ ተሽከርካሪ ሰራ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 7፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋና የክዋሜ ንክሩማህ የሳይንስና ቴክሎጂ ቴክኖሎጂ በፀሃይ ሃይል የሚንቀሳቀስ ተሸከርካሪ ሰርቷል፡፡

ከአካባቢ ጋር ተስማሚ የሆነችው ተሽከርካሪ ባለአራት እግር መሆኗ ተነግሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው መኪናዋን የሰራው ከሙኒክ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ነው ተብሏል።

የክዋሜ ንክሩማህ የሳይንስ እና ቴክሎጂ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢ ብክለት የማይፈጥር የቴክሎጂ ፈጠራ የሆነች ተሸከርካሪ በመስራት በአፍሪካ ቀዳሚ ዩኒቨርሲቲ ይሆናልም ነው የተባለው።

በፀሐይ ሃይል የምትሰራው ተሽከርካሪ አሁን በሙከራ ላይ ስትሆን፥ ደረጃዋን የጠበቀች ተሽከርካሪ ለማድረግ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክዋሲ ኦቢሪ-ዳንሶ ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ቴክኖሎጂ ፈጠራ ላይ ለሚሰራቸው ምርምሮች ተጨማሪ ድጋፍ እንዲደረግለት ጠይቋል፡፡

ከዚህ ቀደም በፈረንጆቹ 2016 የካቲት የኡጋንዳ ኩባንያ በፀሃይ ሃይል የሚሰራ አውቶብስ ማስተዋወቁ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡-ሲ ጅ ቲ ኤን