ማይክሮሶፍት በሚሊየን የሚቆጠሩ የኤሌክትሮኒክስ መፅሀፍቶችን በነፃ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 6፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ማይክሮሶፍት በየዓመቱ ሀምሌ ወር ላይ በነፃ የሚለቃቸውን በርካታ የኤሌክትሮኒክስ መፅሀፍቶች (E-Books) ዘንድሮም አቅርቧል።

የማክሮሶፍት የሽያጭ ዳይሬክተር አሪስ ሊግማን ዘንድሮም በሚሊየን የሚቆጠሩ ነጻ የኤሌክትሮኖክ መፅሀፍቶቹን ለተጠቃሚዎች መቅረባቸውን ይፋ አድርገዋል።

ዳይሬክተሩ እንደሚናገሩት፥ ማይክሮሶፍት ኤሌክትሮኒክስ መጽሀፍቶችን በነፃ ማቅረብ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፤ የሚመጡ ምላሾችም አበረታች ናቸው ብለዋል።

ዘንድሮም በርካታ የኤሌክትሮኒክስ መፅሀፍት (E-Books) ቀርበዋል ያሉት ዳይሬክተሩ፥ መፅሀፍቱን የሚፈልጉ ሰዎችም በቀላሉ የሚፈልጉትን ለይተው እንዲያወርዱ

(ዳወንሎድ እንዲያደርጉ) ተደርጎ ነው የተዘጋጀውም ብለዋል።

ማክሮሶፍት በነፃ ካቀረባቸው መጽሀፍቶች ውስጥም፦

E-Books For Windows 10, Windows Server

E-Books For PowerShell

E-Books For Azure

E-Books For Cloud

E-Books For Microsoft Office 2013, 2016, and 365

E-Books For Power BI

E-Books For Microsoft SharePoint

E-Books For SQL Server

E-Books For Microsoft System Center ይገኙበታል።

መፅሀፍቶቹን በPDF ፣ EPUB እና MOBI ፎርማቶች ማውረድ የምንችል ሲሆን፥ የኤሌክትሮኒክስ መፅሃፍቶችን ለየብቻ እንጂ አንድ ላይ በብዛት ማውረድ እንችለም ተብሏል።

መፅሀፍቶቹን ለማግኘት ይህንን መስፈንጠሪያ (ሊንክ) ይጫኑ ፦ Microsoft’s Free E-Book Giveaway

ምንጭ፦ https://fossbytes.com