ዴል ያለገመድ ሀይል የሚሞላ ላፕቶፕ ለሽያጭ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 6፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዴል በዓለም ላይ የመጀመሪያው ነው የተባለውን ያለ ኤሌክትሪክ ገመድ ሀይል የሚሞላ (ቻርጅ የሚደረግ) ላፕቶፕ ኮፕውተሩን ለሽያጭ አቅርቧል።

ላፕቶፕ ኮምፒውተሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የተደረገው በጥር ወር ላይ በተደረገ የቴክኖሎጂ አውደርዕይ ላይ ሲሆን፥ ኩባንያው አሁን ላይ ላፕቶፑን ለገበያ አቅርቧቸዋል።

ዴል ያለ ገመድ ቻርጅ የሚደረግ ላፕቶፑን “WiTricity” ከተባለ የአሜሪካ ኩባንያ ጋር በጋራ በመሆን የሰራው መሆኑም ተነግሯል።

ዴል ላቲቲዩድ 7285 የሚል መጠሪያ የተሰጠው ላፕቶፕ ኮምፒውተሩ ኢንቴል “Core i5-7Y54 processor” የሚጠቀም ሲሆን፥ 128 ጊጋ ባይት ውስጣዊ የመረጃ መያዣ ቋት እና 8 ጊጋ ባይት ራም አለው።

12 ነጥብ 3 ኢንች የስክሪን ስፋት ያለው ኮምፒውተሩ ዊንዶውስ 10 ሆም ኤፕሬቲንግ ሲስተምን ይጠቀማል።

በተጨማሪም ዋይ ፋይ እና ብሉቱዝ 4 ነጥብ 2ን ጨምሮ በርካታ አገልግሎቶችን መስጠት የሚችል መሆኑም ታውቋል።

ዴል ላቲቲዩድ 7285 ላፕቶፕ ኮምፒውተር የተቆረጠለት የመሸጫ ዋጋም 1 ሺህ 199.99 የአሜሪካ ዶላር ነው የተባለው።

ዴል አዲሱን ገመድ አልባ ላፕቶፕ ኮምፒውተሩን በድረ ገጹ ላይ በይፋ ለሽያጭ ማቅረቡም ተገልጿል።

ምንጭ፦ https://fossbytes.com