ጎግል “ጎግል ፎር ጆብስ” የተባለ የስራ ማፈላለጊያ ገጽ አቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11 ፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቴክኖሎጂው ዓለም መረጃን በማፈላለግ በብዛት ጥቅም ላይ የሚውለው ጎግል ለስራ ፈላጊዎች መልካም ዜና አለኝ ብሏል።

ኩባንያ ስራ ፈላጊዎች በቀላሉ ስራን ለማፈላለግ የሚረዳ “ጎግል ፎር ጆብስ (Google For Jobs)” የተባለ አዲስ አገልግሎት ማቅረቡንም አስታውቋል።

የጎግል ስራ አስፈጻሚ ሰንደር ፒቻይ፥ አገልግሎቱ ስራ የሚፈልጉ ሰዎች በቀላሉ ወደ ገጹ በመግባት የሚፈልጉትን የስራ አይነት ገጹ ላይ በሚያስገቡበት ጊዜ ተገቢ የሆኑ መረጃዎች እንዲደርሳቸው ያደርጋል ብለዋል።

ጎግል ለዚህ አገልግሎት ይረዳው ዘንድም የስራ ማፈላለጊያ ድረ ገጽ ከሆኑት ሊንክዲን፣ ፌስቡክ፣ ኬረርቢዩልደር ሞንስተር እና ግላስዶርን ጋር በጋራ እንደመሚሰራም ተገልጿል።

“ጎግል ፎር ጆብስ” በገጹ ላይ ስራ የሚፈልጉ ሰዎች ምን አይነት ሰዎች እንደሆኑ እና ከዬት እንደሚፈልጉ ማጣራት ይችላል ተብሏል።

በዚህም ፈላጊው ባለበት አድራሻ እና የስራ አይነት የወጡ የስራ እድሎችን ለይቶ የሚያቀርብ መሆኑም ተገልጿል።

“ጎግል ፎር ጆብስ” በጠቃዩቹ ሳምንታት ውስጥ በአሜሪካ በሙከራ ደረጃ ስራ እንደሚጀምርም ኩባንያው አስታውቋል።

ምንጭ፦ https://fossbytes.com