የቻይናው ባይዱ ኩባንያ ያለ አሽከርካሪ የሚሰሩ የመኪና ቴክኖሎጂዎችን ለማጋራት ዝግጅ መሆኑ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይናው ግዙፉ ኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ኩባንያ ባይዱ ሹፌር ሳይኖር በእራሳቸው ሚነዱ መኪናዎች ቴክኖሎጂ ለማጋራት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ኩባንያው የአሁኑ እርምጃው ያለ ሰው አሽከርካሪ በእራሳቸው የሚነዱ መኪናዎች ቴክኖሎጂ እድገትን እንደሚያፋጥን ነው የገለጸው ፡፡

“አፖሎ“ ተሰኘው ይህ ፕሮጀክት ሶፍትዌሮችን፣ሃርድዌሮችን እና የዳታ አግልግሎቶችን ለሌሎች በተለይ ለመኪና ፋብሪካዎች ለማጋራት ዝግጁ መሆኑን ነው የተናገረው፡;

ሌሎች ኩባንያዎች ማለትም እንደ ቴስላ እና ጎግል ያሉት ኩባንያዎች ግን በመስኩ ያሉ ቁልፍ ሚስጥሮችን እና ያበለጸጉትን ቴክኖሎጂ ለማጋራት ፍቃደኛ አይደሉም፡፡

ባይዱ የቻይናው ጎግል ተብሎ የሚጠራ ግዙፍ የኢንተርኔት ኩባንያ ሲሆን፥ ያለ አሽከርካሪ በራሳቸው የሚነዱ ተሸከርካሪ ዎችን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2015 ጀምሮ እየሰራ ይገኛል፡፡

በኩባንያው ቴክኖሎጂ በቅድሚያ የሚጠቀሙት ቢያንስ 20 የቻይና የመኪና ፋብሪካዎች መሆናቸው ተዘግቧል፡፡

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 የባይዱን ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መኪናዎች በቻይና መንገድ ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፦ቢቢሲ

 

በእስክንድር ከበደ