የአለም ምርጥ ጥንታዊ የሥነ-ጽሁፍ ስራዎች በኢንተርኔት አማካኝነት በነጻ የምታገኙበት ድረ-ገጽ


አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ክላሲክ ሪደርስ (Classic Readers ) ድረ-ገጽ በአለማችን የዝነኛ ደራሲያን ስራዎችን በኢንተርኔት አማካኝነት በነጻ አውርደው ከሚጠቀሙባቸው ተወዳጅ ድረ-ገጽ አንዱ ነው፡፡

በድረ-ገጹ ጥንታዊ እና ዘመናዊ የልብወለድ መጽሃፍት፣አጫጭር ልብወለዶች፣የመድረክ ትያትሮች ፣ኢ-ልብወለድ መጽሃፍት ፣ለወጣት አንባቢያን የሚሆኑ የሥነ-ጽሁፍ ስራዎች እና ልዩ ልዩ የኪነጥበብ ድርሰቶች ይገኛሉ፡፡

የክላሲክ ሪደርስ ድረ-ገጽ መስራቾች እንደሚሉት፥ ድረ-ገጹ እሰከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ ለሚማሩ እና መምህራን ለትምህርት እና መዝናኛነት የሚጠቅሙ መጽሃፍት እና ልዩ ልዩ የጥንታዊ ስነጽሁፍ ስራዎችን አካቷል፡፡

የሼክስፒር ፣ የዶስቶቪስኪ ፣ቺኮቭ ፣ቶልስቶይን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት ታዋቂ ደራሲን ስራዎች ተካተውበታል፡፡
የሚፈልጉትን መጽሃፍ በርዕስ እና በደራሲ በመፈለግ በቀላሉ ማግኘት ይቻላል፡፡

ድረ-ገጹን http://www.classicreader.com በሚል በመፈለግ የፈለጉትን አውርደው ለመማሪያነት ፣ማስተማሪያነት እና መዝናኛነት መጠቀም ይቻላል፡፡

ምንጭ፦ክላሲክ ሪደርስ

 

በእስክንድር ከበደ