ያሁ በሩብ ዓመት ያገኘው ገቢ በ22 በመቶ መጨመሩን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ያሁ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ያገኘው ገቢ በ22 ነጥብ 1 በመቶ ከፍ ማለቱን አስታወቀ።

እንደ ያሁ ገለፃ ለገቢው መጨመር በምክንያትነት ከተቀመጡት ውስጥ፥ ከተለያዩ የማህበራዊ ትርስስር ድረ ገጾች እና የሞባይል ስልኮች የቪዲዮ ማስታወቂያዎች ይገኙበታል።

በመጀመሪያው ሩብ አመትም በእነዚህ አገልግሎቶች ብቻ በአጠቃላይ 529 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ማግኘቱን ነው ኩባንያው ያስታወቀው።

በዚህም ያሁ ያገኘው ገቢ ከ1 ነጥብ 09 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ወደ 1 ነጥብ 33 ቢለየን የአሜሪካ ዶላር ከፍ ማቱ ነው የተነገረው።

ምንጭ፦ www.reuters.com