ኖኪያ ሁለት አዳዲስ ስልኮቹን ለገበያ ሊያቀርብ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 11 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ከረጀም ጊዜ በኋላ ወደ ተንቀሳቃሽ ስልክ ገበያው የተመለሰው ኖኪያ አሁን ላይ አዳዲስ ምርቶችን በተደጋጋሚ እያስተዋወቀ ነው።

ገበያውን በድጋሚ ከተቀላቀለ ወዲህም ሶስት አዳዲስ ምርቶቹንና የቀድሞ የኖኪያ ምርቶቹን ወደ ገበያ ይዞ ተመልሷል።

አሁን ደግሞ ኖኪያ 8 እና ኖኪያ 9 የተሰኙ ስልኮቹን ለገበያ ሊያቀርብ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

አዲሶቹ ምርቶች የዘመኑን ቴክኖሎጅ የተጠቀሙ እንደሆኑም ነው መረጃዎች የሚያሳዩት።

ሁለቱም የኖኪያ ምርቶች በአንድሮይድ 7 ነጥብ 0 ስሪት የሚመጡ ናቸው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም የፊት ለፊት 12 ሜጋ ፒክስል ካሜራና የጀርባ 24 ሜጋ ፒክስል ካሜራ ይኖራቸዋልም ነው የተባለው።

የስክሪን መጠናቸው ደግሞ ኖኪያ 8 ስልክ 5 ነጥብ 7 ኢንች ሲኖረው፥ ኖኪያ 9 ደግሞ 5 ነጥብ 5 ኢንች ስፋት እንዳለው ተገልጿል።

ለተገልጋዮች እንዲመቹ ተደርገው የተሰሩት አዲሶቹ የኖኪያ ምርቶች 6 ጊጋ ባይት ራም አላቸው።

ውስጣዊ የመያዝ አቅማቸው ደግሞ በ64 ጊጋ ባይት በ128 ጊጋ ባይት እንደሚሆንም መረጃው ያመለክታል።

ስልኮቹ መቼ እና በምን ያክል ዋጋ ወደ ገበያ እንደሚወጡ ግን የተገለጸ ነገር የለም።

 

 

 

ምንጭ፦ techworm.net