ቤጂንግ የመፀዳጃ ቤት ወረቀት ስርቆትን ለመቆጣጠር ካሜራ መትከል ጀመረች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 11 ፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይና የመፀዳጃ ቤት ስርቆትን ለመቆጣጠር የሚያስችላትን የፊት ገጽታን የሚቀርፅ ሉ-ሮል የተሰኘ የሶፍትዌር ካሜራ በአንድ በርካታ ተጠቃሚዎች ባሉበት መፀዳጃ ቤት ተክላለች፡፡

ቤጂንግ ውስጥ የሚገኘው ቲያንታን ፓርክ ከፍተኛ ጎብኝዎችን በማስተናገድ ይታወቃል፡፡

በዚህ መዝናኛ ስፍራ በሚገኙ መፀዳጃ ቤቶች በርካታ ተጠቃሚዎች ለተፈጥሮ ጥያቄያቸው ምላሽ ይሰጣሉ።

ሆኖም የመፀዳጃ ቤቱን ወረቀት የሚሰርቁ ሰዎች ከመጠን በላይ የሆነ ለስላሳ ወረቀት ስለሚወስዱ፥ አንዳንድ ሰዎች በቂ ወረቀት እንደማያገኙ ቅሬታ እያቀረቡ መሆናቸውን ቻይና ሬዲዮ ኢንተርናሽል ዘግቧል፡፡

ሙሉውን ወረቀት ደብቀው የሚወስዱ በመኖራቸው በ20 ደቂቃ ውስጥ ምንም ወረቀት በመፀዳጃ ቤቱ ውስጥ የማይገኝበት ወቅት እንዳለ ነው የተጠቀሰው፡፡

toilet-paper-thieves-beijing-1.jpg

ለዚህም መፍትሔ ይሆን ዘንድ ወደ መፀዳጃ ቤቱ የሚያመሩ ሰዎች በቅድሚያ የፊት ገጽታቸው በሉ-ሮል(loo-roll) የካሜራ ሶፍትዌር ተቀርጾ እንዲገቡ እየተደረገ ነው።

ይህን ተከትሎ የሚፀዳዱት ሰዎች በካሜራ እይታ ውስጥ ሆነው ማሽኑ 60 ሳንቲሜትር ርዝመት ያለው ለስላሳ ወረቀት ይሰጣቸዋል፡፡

chinadaily.jpg

ሌላ ተመሳሳይ ገፅታ ያለው  በዘጠኝ ደቂቃ ውስጥ የመጠቀሚያ ለስላሳ ወረቀት ወስዶ የነበረ ሰው እንደ አዲስ ለመውሰድ ቢመጣ ሶፍትዌሩ አይሰጠውም ነው የተባለው፡፡

ቤጂንግ ይህን ያደረገቺው የጎብኝዎች ቁጥር ከመብዛቱ እና በመፀዳጃ ቤቱ ውስጥ የተቀመጠውን ወረቀት ለግል ጥቅማቸው ወደ ቤት ይዘው የሚሄዱ ሰዎች በመኖራቸው ቁጥጥሩን ለማጥበቅ መሆኑ ተነግሯል፡፡

 

 

ምንጭ፡- www.china.org.cn