ትዊተር በርካታ አገልግሎቶችን በውስጡ የያዘ የቀጥታ ስርጭት አገልግሎት ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሁኑ ጊዜ በርካታ የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጾች የቀጥታ ስርጭት ዓለምን ለመቆጣጣር የሚደርጉት ፉክክር እየከረረ መጥቷል።

ትዊተርም በዚህ ፉክክር ውስጥ ቀዳሚ ለመሆን አዳዲስ ነገሮችን ይዞ እንደሚመጣ ነው እየተነገረ ያለው።

አዱሱ የቀጥታ ስርጭት አገልግሎት በቀጣዩ ሳምንት በአሜሪካዋ ሳን ፍራንሲስኮ ይፋ እንደሚደረግ ተነገረ ሲሆን፥ አገልግሎቱም በእለቱ እንደሚጀመር ይጠበቃል።

የትዊተር የቀጥታ ስርጭት አገልግሎት “አፕሊኬሽን ፕሮግራም ኢንተርፊራንስ (API)” የሚባል ሲሆን፥ የሚዲያ ኩባንያዎች በቀጥታ በትዊተር ላይ ስርጭታቸውን እንዲያስተላልፉ የሚረዳ ነው።

“አፕሊኬሽን ፕሮግራም ኢንተርፊራንስ (API)” የሚዲያ ተቋማት ከስማርት ስልክ ይልቅ ፕሮፌሽናል ካሜራዎቻቸውን በመጠቀም በትዊተር ላይ በቀጥታ እንዲያሰራጩ የሚያስችል መሆኑም ተጠቁሟል።

ፕሪስኮፕ

ትዊተር አሁንም ቢሆን የቀጥታ ስርጭት አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን፥ ይህም “ፕሪስኮፕ” በሚባል መተግበሪያ አማካኝነት ነው የሚሰራው።

በመተግበሪያው የሚዲያ ተቋማትም የቀጥታ ስርጭትን የሚያስተላልፉ ሲሆን፥ ሚዲያዎች “ፕሪስኮፕ ፕሮድዩሰር” በሚባል መተግበሪያ አማካኝነት ነው ጥራት ያለው የቀጥታ ስርጭትን በትዊተር ላይ ለማስተላለፍ የሚጠቀሙት።

periscope_producer.jpg

አዲሱ “አፕሊኬሽን ፕሮግራም ኢንተርፊራንስ (API)” ግን የሚዲያ ተቋማት “ፕሪስኮፕ ፕሮድዩሰር” አገልግሎት ሙሉ በሙሉ እንደተው የሚያደርግ ነው።

ትዊተር “በAPI” የቀጥታ የቪዲዮ ስርጭት ከግለሰቦች ይልቅ ትላልቅ የሚዲያ ተቋማት ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑም ተነግሯል።

ምንጭ፦ www.dailymail.co.uk