ከ10ሺህ በላይ በኢንተርኔት አማካኝነት ነጻ ትምህርታዊ ቪዲዮዎች እና ገለጻዎችን የሚያገኙበት ድረ-ገጽ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ካን አካዳሚ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2006 በትምህርት ባለሙያው ሳልማን ካን የተመሰረተ የትምህርት ተቋም ነው፡፡
የካን አካዳሚ ትምህርትን ለሁሉም ተደራሽ ማደረግ ዋነኛ ግቡ አድርጎ መቋቋሙን መስራቾቹ ይናገራሉ፡፡

የአካዳሚው አጫጭር ገለጻዎችን በዩ ቲዩብ ቪዲዮዎች በማዘጋጀት ገላጭ ትምህርቶችን ይሰጣል፡፡

በድረ-ገጹ ለመምህራንና አሰልጣኞች ተጨማሪ ሙከራዎች ፣የቤት ስራዎች እና ተግባራዊ ልምምዶች አካቷል፡፡

ሁሉም ማጣቀሻ እና ይዘቶች ለሁሉም ተጠቃሚዎች በቀላሉ እንዲያገኙ የተዘጋጀ ነው ፡፡

በአካዳሚው ድረ-ገጽ በፈለጉት ደረጃ ሂሳብ፣ሳይንስ፣ኢኮኖሚክስ፣ታሪክ እና በርካታ ትምህርቶችን በእጆ መዳፍ በቀላሉ የሚያገኙበት እውቀት ማሳደጊያ መድረክ ነው፡፡

የድረ-ገጹ ይዘቶች ባብዛኛው በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ሲሆን፤በሌሎች ቋንቋዎች እንደ በስፓኒሽ ፣ፖርቱጊዝ ፣ቱርኪሽ ፣ፈረንሳይኛ እና ህንደኛ የተዘጋጁ ናቸው፡፡

እንደ አውሮፓውያኑ አቖጣጠር በ2010 አዳዲስ ኮርሶችን ለመፍጠር እና ወደ ይዘቶቹን ሌሎች ቋንቋዎች ለመተርጎም ጎግል 2 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ለግሶታል፡፡

በ2015 ኤቲ ኤንድ ቲ የተሰኘው ግዙፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያ 2 ነጥብ 25 ሚሊየን ዶላር ለካን አካዳሚ ለግሷል፡፡

የአካዳሚው የርቀት ትምህርት የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች በዩ ቲዩብ ቪዲዮ በተቀረጹ እና ኤሌክትሮኒክ ጥቁር ሰሌዳ ልክ በክፍል ውስጥ መምህር ገለጻ በሚያደርግበት ስልት የተቃኘ ነው፡፡

ካን አካዳሚ በአለም ላይ ለ1 ቢሊየን ሰዎች ትምህርት የሰጠ ሲሆን፤በዚህ የኢንተርኔት መድረክ በወር 40 ሚሊየን ተማሪዎች እና 2 ሚሊየን መምህራን ይጠቀሙበታል፡፡

የአካዳሚው ትምህርታዊ ይዘቶች በ36 የአለማችን ቋንቋዎች በበጎ ፍቃደኞች እየተተረጎሙ ይገኛሉ፡፡

የካን አካዳሚ ድረ-ገጽን www.khanacademy.org ወይም በጎግል መፈለጊያ Khan Academy ብለው በመፈለግ መጠቀም ይችላሉ፡፡

ምንጭ፦ www.khanacademy.org


ተተርጉሞ የተጫነው፦በእስክንድር ከበደ