ጀርባው አንድሮይድ ስማርት ስልክ የሆነው የአይ ፎን ስልክ ሽፋን

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጀርባው በኩል የአንድሮይድ ስልክ የተገጠመለት የአይ ፎን ስልክ መያዣ ተሰርቷል።

የአንድሮይድ እና የአይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን የሚጠቀሙ ስማርት ስልኮች አመራረታቸውም ይሁን የሚሰጡት አገልግሎት ላይ ልዩነቶች አሉት።

ሆኖም ግን የእስራኤሉ ኩባንያ ሁለቱንም አይነት ስልኮች በአንዴ መጠቀም የሚያስችል አዲስ ፈጠራ ይዞ መምጣቱን አስታውቋል።

ይህም የአይፎን ስልክ መያዣ ሲሆን፥ መያዣው በጀርባው በኩል የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚጠቀም ስማርት ስልክ ነው።

ኤስቲ ኢንክ የተባለው ኩባንያ፥ ያስተዋወቀው ይህ የአይፎን ስልክ መያዣ እና “አይ (Eye)” የሚል መጠሪያ ተሰጥቶታል።

eye_iPhone_case.jpg

በመያዣው ላይ የተገጠመው አንድሮይድ ስማርት ስልክ 5 ኢንች የስክሪን ስፋት፣ ሁለት ሲም ካርድ የሚቀበል እንዲሁም እንደ ብሉቱዝ እና ዋይ ፋይ ያሉ አገልግሎቶች የሚያስጠቅም ነው።

የአንድሮይድ ስማርት ስልኩ ዝርዝር፦

  • octa-core ARM Cortex A53 CPU
  • Android Nougat 7.1
  • 5-inch AMOLED display
  • 2GB DDR3 memory
  • 2800 mAh battery
  • dual-sim LTE support
  • microSD slot
  • Bluetooth 4.2
  • WiFi ac, and a headphone jack

ኤስቲ ኢንክ ኩባንያ “አይ” የተባለውን የአይ ፎን ስልክ መያዣ እና አንድሮይድ ስማርት ስልክ በስፋት አምርቶ ገበያ ላይ ለማወዋልም ገንዘብ የማሰባሰብ ቅስቀሳ ጀምሯል።

ምርቱም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በነሃሴ ወር 2017 በስፋት ተመርቶ ለገበያ ይቀርባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

ምንጭ፦ https://fossbytes.com

በሙለታ መንገሻ 

android_ads__.jpg