ኦፕን ካልቸር የተሰኘ ጠቃሚ የባህልና ትምህርት ሚዲያ ድረ-ገጽ እንጠቁሞት

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 6 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) (Open Culture) ድረ-ገጽ በስታንፎርድ ዩኒቪርሲቲ የርቀት ተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም ዳይሬክተር እና ረዳት ዲን ዳን ኮልማን እንደተመሰረት ይነገራል፡፡

ድረገጹ 950 ነጻ ኦንላይን የርቀት ኮርሶች በታዋቂ የአለማችን ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙበት ሲሆን ፤675 ጥንታዊ ፊልሞችን ጨምሮ በርካታ ዘጋቢ ፊልሞችን ያገኙበታል፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ 550 በድምጽ የተተረኩ መጽሃፍት በቀላሉ በማውረድ መጠቀም ሚቻል ሲሆን፤ ከ200 በላይ ለልጆች የሚሆኑ ትምህርታዊ መረጃዎችም ያገኛሉ፡፡

ድረ-ገጹ ከአጸደ ህጻናት እስከ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ጠቃሚ የሆኑ ማጣቀሻ መጽሃፍትን በመያዙ አንባቢዎች አውርደው መጠቀም ይችላሉ ፡፡

በዚህ ድረገጽ 1 ሺህ 200 ነጻ ኮርሶች፣265 ነጻ ዘጋቢ ፊልሞች እና በኦስካር ሽልማት ያገኙ አጫጭር ፊልሞች እንዲሁም በደምጽ የሚነበቡ መጽሃፍት(Audio Books) ያገኙበታል፡፡

ድረ-ገጹን www.openculture.com ወይም በጎግል Open Culture ብለው በመፈለግ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ምንጭ፦ ኦፕን ካልቸር

ተተርጉሞ የተጫነው፦በእስክንድር ከበደ