የስልክ ባትሪዎችን ህይወት ሊያረዝሙ የሚችሉ 5 ጠቃሚ ምክሮች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የስማርት ስልክዎ ባትሪ በፍጥነት እያለቀ አስቸግሮዎታል?

እንግዲያውስ የሚከተሉትን አማራጮችን በመጠቀም የባትሪ ህይወትን ማርዘም ይችላሉ፡፡

1. ለወራት ያልተቀሙባቸውን አፕሊኬሽኖች ወይም መተግበሪያዎች ማጥፋት

ስልካችን ላይ ጭነናቸው ነገር ግን ለወራት ምንም ጥቅም ላይ ሳናውላቸው ነገር ግን ኢንተርኔት በሚጠቀሙበት ጊዜ ማሳወቂያ (ኖቲፊኬሽን) እና የመሳሰሉትን የሚልኩ መተግበሪያዎች (አፕሊኬሽኖች) የባትሪያችን ህይወት ሊያሳጥሩት ይችላሉ፡፡

battry_1.png

በመሆኑም እነዚህን መተግበሪያዎች ከስልካችን ላይ ማጥፋት የባትሪ ህይወት ከማራዘም ባለፈ ከአላስፈላጊ የኢንተርኔት ወጪ ሊያድነን ይችላል፡፡

2. ጠቃሚ ያልሆኑ መተግበሪያዎችን Background data እንዳይጠቀሙ ማድረግ

ኢንተርኔት በሚጠቀሙበት ጊዜ Background data የሚጠቀሙ አፕሊኬሽኖችን ሴቲንግ ውስጥ በመግባት Background data እንዳይጠቀሙ በማድረግ የባትሪ እድሜን ማራዘም እንችላለን።

batt_2.png

እናም ብዙ ጊዜ የማይጠቀሙባቸውን አፕሊኬሽኖችን ወይም መተግበሪያዎች በመምረጥ Background data እንዳይጠቀሙ ማድረግ ይኖርብናል።

3. ብዙ መተግበሪያዎችን በአንድ ጊዜ ከመዝጋትና መክፈት መቆጠብ

ብዙ ጊዜ እንደነ ኦፔራ ሚኒ፣ ፌስቡክ የመሳሰሉ መተግበሪያዎችን ተጠቅመን ስንጨርስ ዘግተን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ መልሰን እንከፍታለን፡፡

batt_3.png

ይህን ተግባር በተደጋጋሚ ባደረግን ቁጥር ለሞባይላችን ባትሪ ጠንቅ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ስለሆነም ከተጠቀምን በኋላ የ“ሆም” ቁልፉን ተጠቅመን መውጣት ሌላ ጊዜ መጠቀም ስንፈልግ ሞባይላችን ካቆመበት እንዲቀጥል ያደርገዋል፡፡
ይህም የሞባይላችንን ባትሪ እድሜን ያስቀጥላል።

4. ንዝረት ማጥፋት

የስልክ ጥሪ በድምፅ (ሪንግቶን) ብቻ መጠቀም ለብዙዎቻችን አስቸጋሪ እንደሚሆን ግልፅ ነው።

ሆኖም ግን የስልካችን ባትሪ ህይወት ማስረዘም ሀሳብ ካለን የስልካችን ቫይብሬሽን ማጥፋት ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡

batt_4.png

ይህንንም ለማድረግ ሴቲንግ ውስጥ የድምፅ አማራጭ ውስጥ በመግባት ቫይብሬሽኑን ማጥፋት ያስፈልጋል፡፡

5. ብሉቱዝ ማጥፋት

አብዛኞቻችን የምንፈልገውን ነገር ከወዳጆቻችን ጋር ብሉቱዝን በመጠቀም ከተላላክን በኋላ ብሉቱዛችንን ማጥፋት እንዘነጋለን፤ ይህ ደግሞ ለባትሪያችን ህይወት ማጠር እንደ ምክንያት ይነሳል፡፡

batt_5.png

ለዚህም እንደአማራጭነት የቀረበው ሁልጊዜ ብሉቱዛችን መጥፋቱን ማረጋገጥ እንዲሁም ከሰዎች ጋር ፋይሎችን ከተላላክን በኋላ ወዲያውኑ ማጥፋትን አለመዘንጋት ነው፡፡

 

ምንጭ፦ ታይም መፅሄት