ኖኪያ 3310 ዳግም ወደ ገበያ ሊመለስ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 7፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኖኪያ 3310 በርካቶቻችን ለመጀመሪያ ጊዜ የያዝነው የሞባይል ስልክ እንደሆነ ለመገመት አያዳግትም።

ታዲያ በዓለም ዙሪያ በርካቶች የተጠቀሙበት ኖኪያ 3310 በአዲስ መልክ ዳግም ወደ ገበያው ሊመለስ መሆኑን ኤች.ኤም.ዲ ግሎባል ኩባንያ አስታውቋል።

ኖኪያ 3310 በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለገበያ ይቀርባል የሚሉ መረጃዎችም ከወዲሁ እየተሰሙ ነው።

ኖኪያ 3310 የመሸጫ ዋጋም የተቆረጠለት ሲሆን፥ የአንዱ ስልክ የመሸጫ ዋጋ 63 የአሜሪካ ዶላር መሆኑም ተነግሯል።

ኖኪያ 3310 ለመጀመሪያ ጊዜ የሞባይል ገበያውን የተቀላቀለው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2000 ነበር።

በጊዜውም ኖኪያ 3210 በመተካት ገበያውን የተቀላቀለ ሲሆን፥ በገበያው ውስጥም ከፍተኛ ስኬትን ያስመዘገበ የሞባይል ስልክ መሆኑ ይታወሳል።

ኖኪያ 3310 በጥንካሬው፣ በስኔክ ጌም መጫወቻው እና በረጅም የባትሪ እድሜው ነው በርካቶች ዘንድ የሚታወቀው።

የኖኪያ ኩባንያ ከኖኪያ 3310 የሞባይል ስልክ በተጨማሪም፥ ሁለት አዳዲስ አንድሮይድ ኖኪያ ስማርት ስልኮች ለገበያ እንደሚያቀርብ ተነግሯል።

አዳዲሶቹ ስማርት ስልኮችም ኖኪያ 6 እና ኖኪያ 5 ስማርት ስልኮች ናቸው ተብሏል።

ምንጭ፦ https://fossbytes.com

android_ads__.jpg