ዜድ ቲ ኢ 3 ሺህ ሰራተኞቹን ሊቀንስ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 1 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው የስልክ አምራች ኩባንያ ዜድ ቲ ኢ 3 ሺህ ሰራተኞችን ሊቀንስ ስለመሆኑ ተናግሯል።

ይህም ኩባንያው አለም ላይ ካለው 60 ሺህ የሰራተኞች ቁጠር 5 በመቶውን ይሸፍናል ተብሏል።

ከዚህ ውስጥ በቻይና በሚገኙ ቢሮዎቹ ከ20 በመቶ በላዩን ሲቀንስ፤ 10 በመቶዎቹ በዚህ ወር መጨረሻ ከስራ መሰናበታቸውን እንደሚያውቁም ኩባንያው ገልጿል።

ኩባንያው እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከአሜሪካ መንግስት የንግድ ማዕቀብ እንደሚጣልበት ከተነገረው በኋላ ነው።

የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ዛሆ ዢያንሚንግ ኩባንያው በ31 አመት የስራ ቆይታው ከፍተኛውን ችግር መጋፈጡን በአዲሱ አመት መባቻ ገልጸው ነበር።

በዚህም የሂሳብ ሪፖርቱንና አስተዳደራዊ መዋቅሩን ማሻሻል ቀጣይ ስራው እንደሚሆንም ተናግረዋል።

በ2017 ከተቋሙ ስትራቴጅ ጋር አብረው የማይሄዱ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የቢዝነስ ዘርፎች ይዘጋሉም ነው ያሉት።

ከዚህ ባለፈም እነዚህን ቢዝነሶች በማጠፍ፣ ለጊዜው በማቆምና ከሌሎች ጋር በማዋሃድ የኩባንያውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ይሰራልም ብለዋል።

ዜድ ቲ ኢ ከቻይና ኩባንያዎች መካከል በሃገረ አሜሪካ በዘርፉ ተፅዕኖ በመፍጠር ብቸኛው ስለመሆኑ ይነገራል።

 

 

ምንጭ፦ ሬውተርስ

android_ads__.jpg