የኤፍ.ቢ.አይ ድረ ገጽ በመረጃ መዝባሪዎች መጠለፉ ተሰምቷል

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ የፌደራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍ.ቢ.አይ) ድረ ገጽ በመረጃ መዝባሪዎች መጠለፉ ተሰምቷል።

ድረ ገጹን ማንነታቸው ያልታወቀ የመረጃ መዝባሪዎች ቡድን የጠለፈው ሲሆን፥ ከተቋሙን ቁልፍ መረጃዎችም በኢንተርኔት ላይ ማሰራጨታቸው ነው የተነገረው።

ሳይበርዜይስት የተባለ የጠላፊዎች ቡድንም ጠለፋውን ያካሄድኩት እኔ ነኝ ሲልም ሃላፊነቱም መውሰዱ ተሰምቷል።

የሳይበር ጠላፊዎቹ ወደ ድረ ገጹ የሚገባበት ከ150 በላይ መረጃዎቸን፣ የኢሜል አድራሻዎችን እና ኢንሳይክሪፕትድ የሆኑ የይለፍ ቃል (passwords) በኢንተርኔት ላይ ወይም ኦን ላይን መልቀቃቸውም ተነግሯል።

ከዚህ በተጨማሪም የ155 የኤፍ.ቢ.አይ ባለስልጠናት ስም፣ የኢ ሜይል አድራሻ እና የይለፍ ቃል በኢንተርኔት ላይ ተለቋል።

ሳይበርዜይስት ከአድራሻዎቹ እና ከይለፍ ቃሎች በተጨማሪም ተቋሙ የሚጠቀምበትን የተለያዩ ሶፍትዌሮችንም ይፋ አድርጓል።

ሳይበርዜይስት የጠላፊዎች ቡድን FBI.GOV ድረ ገጽ መጥለፉንም ከስክሪን ላይ የተነሱ ፎቶግራፎችን አስደግፎ በትዊተር ገጹ ላይ አውጥቷል ነው የተባለው።

ምንጭ፦ www.techworm.net

android_ads__.jpg