ኖኪያ የመጀመሪያ ስማርት ስልኩን ለገበያ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሞባይል ስልክ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስም እና ዝና ያለው ኖኪያ በአዲስ ስማርት ስልክ ገበያውን ዳግም ተቀላቅሏል።

ኩባንያው በትናንትናው እለተም ኖኪያ 6 የሚል መጠሪያ የተሰጠውን የመጀመሪያውን ስማርት ስልኩን ለገበያ አቅርቧል።

አዲሱ ኖኪያ 6 ስማርት ስልክ 5 ነጥብ 5 ኢንች የስክሪን ስፋት ያለው ሲሆን፥ አዲሱን አንድሮይድ 7.0 ኑጋት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ነው የሚጠቀመው።

ኖኪያ 6 “ኦክታኮር ኩዋልኮም ስናፕድራጎን 430 ፕሮሰሰር” የተገጠመለት ሲሆን፥ 4GB ራም እንዳለውም ተነግሯል።

እንዲሁም በስልኩ ላይ የተገጠመው የመረጃ መያዣ(internal storage) 64GB ሲሆን፥ ሜሚሪ ካርድ በመጠቀም እስከ 128GB ማስፋት ይቻላል።

ኖኪያ 6 ስማርት ስልክ 16 ሜጋ ፒክስል የጀርባ ካሜራ እንዲሁም 8 ሜጋ ፒክስል የፊት ካሜራ ተገጥሞለታል።

ስማርት ስልኩ 3000mAh ባትሪ ያለው ሲሆን፥ ባትሪው ከስልኩ ላይ የሚነቀል መሆኑም ተነግሯል።

ሁለት ሲም ካርዶችን በአንድ ጊዜ የሚቀበለው ኖኪያ 6 ስማርት ስለክ፥ (GSM + CDMA እና GSM + GSM) ሲም ካርዶችን በአንድ ጊዜ ይቀበላል።

Nokia_N6_2.png

ኖኪያ 6 ስማርት ስልክ በትናንትናው እለትም በ246 የአሜሪካ ዶላር በቻይና ገበያ ለሽያቅ መቅረቡን የፊንላንዱ ኩባንያ ይፋ እደርጓል።

የፊንላንዱ ኤች.ኤም.ዲ ኩባንያ እንዳስታወቀው፥ “ስማርት ስልኮቹን በቻይና ይፋ ማድረግ የተፈለገው በቀላሉ በመላው ዓለም ያሉ ደንበኞቻችንን እና የስማርት ስልክ ገበያን ለመድረስ ስለሚያችልን ነው” ብሏል።

ምንጭ፦ www.techworm.net

android_ads__.jpg