የጃፓኑ የኢንሹራንስ ኩባንያ 34 ሰራተኞቹን በሮቦት ተክቷል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከዚህ ቀደም የሰው ልጆች ስራን በማሽኖች ተተክቶ ሲሰራ የሚታወቀው በሳይንሳዊ ልብወለዶች ላይ ነበር።

አሁን ላይ ግን በየጊዜው የሮቦት ቴክኖሎጂው እየረቀቀ፤ ሰዎች የሚሰሩትን ስራ በሮቦቶች የመተካቱ ነገርም እውን እየሆነ ነው።

በዚህ በኩል ደግሞ ደግሞ የጃፓኑ የኢንሹራንስ ኩባንያ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዝ ሲሆን፥ ኩባንያ ሰራተኞቹን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንት ሮቦቶች በመተካት ላይ ነው።

ኩባንያው እስካሁንም በሰዎች ይሰሩ የነበሩ 34 የስራ በደቦችን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንት በሮቦቶች መተካቱንም አስታውቋል።

ፉኮኩ ሙቹዋል ላይፍ ኢንሹራንስ የተባለው ኩባንያው፤ ስራተኞቹን ስራ እያስለቀቀ በአርቴፊሻል ሮቦቶች እየተካ ሲሆን፥ ሮቦቶቹም በበተኩበት ስፍራ ላይ በመሆን ለኢንሹራንስ የተከፈለ ገንዘብን የሚያሰሉ ይሆናል።

ስራውን በሮቦቶች መስራቱም ውጤታማነቱን በ30 በመቶ እንደሚያሳድግለት እምነት እንዳለው ኩባንያው አስታውቋል።

ኩባንያው በሮቦቶች አማካኝነት ስራውን መስራቱ በዓመት ውስጥ 140 ሚሊየን የጃፓን የን ወይም 1 ነጥብ 2 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪን እንደሚቀንስለት ተነግሯል።

ሆኖም ግን የኢንሹራንስ ኩባንያው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንት ሲስተሙን ለማስገጠም 200 ሚሊየን የጃፓን የን የሚያወጣ ሲሆን፥ ለሮቦቶቹ እድሳትም በየዓመቱ 15 ሚሊየን የጃፓን የን ወጪ እንደሚያደረግም ይጠበቃል።

AI_robot_2.jpg

በጃፓን የሚገኙ ሌሎች የኢንሹራንስ ኩባንያዎችም የሰራተኞቻቸውን ስፍራ በሮቦት ለመተካት እንቅስቃሴ ጀምረዋል የተባለ ሲሆን፥ እስካሁንም ሶሰት ኩባንያዎች ሰራተኞቻቸውን በሮቦት ለመተካት አቅድ መያዛቸውም ታውቋል።

ዎርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም ባወጣው ጥናት መሰረት በሮቦቶች እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንት አማካኝነት የዓለምን ኢኮኖሚ ከሚመሩ 15 ሀገራት ውስጥ ብቻ በ5 ዓመታት ውስጥ 5 ነጥብ 1 ሚሊየን ሰዎች ስራ አጥ ይሆናሉ።

ይህም የዓለማችን 65 በመቶውን ሊሸፍን እንደሚችለም ነው በጥናቱ ላይ የተቀመጠው።

ምንጭ፦ www.bbc.com/news

android_ads__.jpg