Fana: At a Speed of Life!

18 ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ205 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 30 ፤2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 18 ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ205 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።

የባንኮቹ እና የፋይናንስ ተቋማቱ  ፕሬዚዳንቶች  እና ተወካዮች ድጋፉን ለአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አስረክበዋል  ።

በኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር አስተባባሪነት 18 ባንኮችን ጨምሮ የኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ205 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ  ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት የፋይናንስ ተቋማቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሀገር መከላከያ ሰራዊቱ  ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል ።

የሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ለሚያደረገው ህግን የሰላም ማስከበር እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ወይዘሮ አዳነች ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ የሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት ያደረጉትን የገንዘብ ድጋፍ ምክትል ከንቲባዋ ለሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ለሆኑት ኮለኔል የኑስ ሙሉ አስረክበዋል ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል

https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.