Fana: At a Speed of Life!

ሩዋንዳ ከአስከፊው የዘር እልቂት በኋላ ዳግም እንድትገነባ ኢትዮጵያ ላበረከተችው አስተዋጽኦ ምስጋና አቀረበች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩዋንዳ ገጥሟት ከነበረው አስከፊው የዘር እልቂት በኋላ ዳግም እንድትገነባ ኢትዮጵያ ላበረከተችው አስተዋጽኦ ምስጋና አቀረበች።

በሩዋንዳ ኪጋሊ የሩዋንዳ ዘር ጭፍጨፋ 30ኛ ዓመት ዛሬ ታስቧል።

በመታሰቢያ ስነ-ስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሌሎች ሀገራት መሪዎች ተገኝተዋል።

የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ሩዋንዳውያን በችግር በነበሩበት ወቅት ላሳዩት አብሮነት አመስግነዋል።

በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በወጣትነት እድሜያቸው የሰላም አስከባሪ በመሆን ሩዋንዳ የዘመቱ መሆናቸውን አንስተው አመስግነዋል።

በአልዓዛር ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.